ስፓርት

በፈረንሳይ ሞንትሪዩል ቱር በተደረገ የ1500 ሜትር ውድድር ድርቤ ወልተጂ አሸነፈች

By Mikias Ayele

June 03, 2022

 

አዲስ አበባ፣ግንቦት 26፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሳይ የ2022 ሞንትሪዩል ቱር በተደረገው የሴቶች 1500 ሜትር ውድድር ድርቤ ወልተጂ ቀዳሚ በመሆን አሸንፋለች፡፡

ድርቤ እርቀቱን 3 ሰዓት ከ59 ደቂቃ 48 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት ነው ቀዳሚ ሆና ማጠናቀቅ የቻለቸው፡፡

በትላንት ምሽቱ የ1500 ሜትር  ውድድር ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት መብሪት መኮንን 2ኛ ሆና ርቀቱን መጨረሷን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነወ መረጃ ያመላክታል፡፡