Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ እና ቱርክ በኢድሊብ አዲስ የተኩስ አቁም ስምምነት ደረሱ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሩሲያና ቱርክ በሶሪያዋ ኢድሊብ የደረሱት የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።

ስምምነቱ ትናንት በሞስኮ በሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና በቱርኩ አቻቸው ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን መካከል የተደረሰ ነው።

ስምምነቱ በቱርክ በሚደገፉት አማጽያን እና በሩሲያ የሚደገፈው የአላሳድ መንግስት ወታደሮች ለሳምንታት የዘለቀ ከባድ ውጊያ ካካሄዱ በኋላ የተደረሰ መሆኑ ነው የተነገረው።

በስምምነቱ መሰረት የሩሲያና የቱርክ ወታደሮች በጋራ የሚቆጣጠሩት አካባቢ እንዲሁም ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ የሚሆኑ ስፍራዎችም ተለይተዋል።

ኢድሊብ በሶሪያ የአማጽያኑ ጠንካራ ይዞታ ስትሆን፥ ስፍራውን ለመቆጣጠር የበሽር አላሳድ ወታደሮች ተደጋጋሚ ጥቃቶችን እየፈጸሙ ይገኛል።

ከስምምነቱ በፊት በፈጸሙት ጥቃትም 60 የሚሆኑ የቱርክ ወታደሮች ለህልፈት መዳረጋቸው ይነገራል።

በአማጽያኑ እና በበሽር አላሳድ ወታደሮች መካከል ያለው ግጭት በአካባቢው ለሰብዓዊ ቀውስ ምክንያት ሆኗል።

ቱርክ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከመደረሱ ቀደም ብሎ ሁለት ወታደሮቿ እንደተገደሉባት ገልጻለች።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በወሰደችው አፀፋዊ እርምጃ 21 የሶሪያ ወታደሮችን መግደሏንና ከባድ መሳሪያችን ማውደሟንም ነው የገለጸችው።

ምንጭ፦ ቢ.ቢ.ሲ

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.