የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ ከአረብ አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር የሁልጊዜ ፍላጎቷ ነው -ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ

By Feven Bishaw

June 03, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የአረብ ሀገራት አምባሳደሮች ምክር ቤት አባላትና የአረብ ሊግ አምባሳደር በጠየቁት መሠረት በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል::

በውይይቱ የአምባሳደሮቹ ዲን፥ ቡድኑ በሚወክሏቸው አገሮችና በኢትዮጵያ መካከል በምክክርና በመግባባት ላይ የተመሰረተውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል::