Fana: At a Speed of Life!

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት በ2ኛ ዙር ያሰባሰባቸውን ከ10 ሺህ በላይ መጻሕፍት አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት በሁለተኛ ዙር ያሰባሰባቸውን ከ10 ሺህ በላይ መጻሕፍት አስረከበ።
 
በአብርሆት ቤተ መጻሕፍት በተከናወነው የርክክብ ስነ ስርዓት ላይ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው፣ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አቤል አዳሙ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ዶክተር ታምራት ኃይሌ እና ከደራሲያን ማህበር ደራሲ አበረ አዳሙን ጨምሮ ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
 
የተበረከቱት መጻሕፍት የሳይንስ፣ ጥበብ፣ ታሪክና የተለያዩ ይዘቶች ያሏቸው ሲሆን፥ በተለያዩ የአገር ውስጥ እና የውጪ ቋንቋዎች የተጻፉ መሆናቸውም በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።
 
ማጽሃፎቹ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሰራተኞች፣ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አድማጭ ተመልካቾች እና አጋሮች የተሰበሰቡ መሆናቸውም ተመላክቷል።
 
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በአንደኛ ዙር 2 ሺህ 400 መጻሕፍት እና በ2ኛ ዙር ከ10 ሺህ መጻሕፍት በላይ፥ በአጠቃላይ ከ12 ሺህ 400 በላይ መጻሕፍትን ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት አበርክቷል።
 
 
በአብርሃም ፈቀደ

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.