Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ በ105 ሚሊየን ብር የተገዙ 510 ሞተር ሳይክሎችን ለክልሎች አከፋፈለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በ105 ሚሊየን ብር የተገዙ 510 ሞተር ሳይክሎችን ለክልሎች አከፋፍሏል፡፡
በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ በተካሄደ ርክክብ ስነ-ስርዓት ላይ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ቁልፎቹን ለክልሎቹ ተወካዮች አስረክበዋል፡፡
ሞተር ሳይክሎቹ የክልሎችን አቅም ለማጠናከር በሁለተኛው ምእራፍ የአንድ ቋት መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮግራም የተገዙ መሆናቸውን አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ተናግረዋል፡፡
ሞተር ሳይክሎቹ ለየክልሎቹ ውሃ፣ ጤናና ትምህርት ቢሮዎች የሚከፋፈሉ ሲሆን÷በአንድ ቋት መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮግራም የሚገነቡ ተቋማት ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ፣ በብልሽትም ጊዜ ጥገና ለማካሄድ አገልግሎት እንደሚሰጡ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም በሁለተኛው የከተሞች መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮግራም አማካኝነት በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ለደረሰበት ለደሴ ከተማ ውሃ አገልግሎት 27 ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተሮች፣ 16 ፕሪንተሮች፣ 2 ላፕቶፖች፣ አንድ ፎቶ ኮፒ ማሽንና አንድ ስካነር መበርከቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.