Fana: At a Speed of Life!

ነዋሪነታቸውን ካናዳ ያደረጉት ኢትዮጵያዊ ለኮምቦልቻ ሆስፒታል 9 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ነዋሪነታቸውን በካናዳ ያደረጉት ኢትዮጵያዊ ለኮምቦልቻ አጠቃላይ ሆስፒታል 9 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ፡፡
 
ድጋፉን ያደረጉት አቶ ከበደ ሃይለማሪያም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት÷ የህክምና ቁሳቁሱ ከቤተሰቦቻቸውና ከጎደኞቻቸው ጋር በመሆን ያሰባሰቡት ነው፡፡
 
አቶ ከበደ ከዚህ በፊት አንድ ኮንቴነር የህክምና ቁሳቁስ ለሆስፒታሉ ድጋፍ ቢያደርጉም አሸባሪው ቡድን እንዳወደመውና እንደዘረፍው ገልጸው÷አሁን ላይ ሆስፒታሉ ከደረሰበት ውድመት እንዲያገግም ተጨማሪ ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
 
የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ከበደ ይመር በበኩላቸው÷ ሆስፒታሉ በሽብር ቡድኑ ህወሓት ከ800 ሚሊየን ብር በላይ ውድመት ቢደርስበትም፤ በመንግስትና በበጎ ፈቃደኛ ግለሰቦች ድጋፍ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡
 
የተደረገው ድጋፍም በሆስፒታሉ ይስተዋል የነበረውን የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተት በእጅጉ እንደሚቀርፍ ነው የገለጹት፡፡
 
የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ወንደሰን ልሳነ ወርቅ÷ አሸባሪው ህወሓት በከተማዋ በሚገኙ የመንግስት ተቋማትና ትልልቅ ፍብሪካዎች ላይ ከ10 ቢሊየን ብር በላይ ውድመት ማድረሱን አስታውሰዋል፡፡
 
አሁን ላይም ተቋማቱ እየተደረገላቸው ባለው ድጋፍ ከደረሰባቸው ጉዳት በማገገም ወደ ስራ እየተመለሱ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
 
በከድር መሀመድ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.