በቡታጅራ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሆስፒታል ተመርቆ ለስራ ክፍት ሆነ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ ለ2 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ነዋሪዎች የጤና አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሆስፒታል ተመርቆ ለስራ ክፍት ሆኗል፡፡
በግል ባለሀብት የተገነባው ይህ ሆስፒታል የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ እና የጤና ሚኒስትር ተወካይና የክሊኒካል ሰርቪስ አገልግሎቶች ዳይሬክተር ዶክተር አባስ ሀሰን በተገኙበት ነው የተመረቀዉ፡፡
ሆስፒታሉ ከ400 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት መሆኑን የሆስፒታሉ ባለቤት ዶክተር ጸጋዬ ዘውዴ በምረቃው ላይ ተናግረዋል፡፡
በዞኑ የመጀመሪያና ከዚህ ቀደም የተሻለ ህክምና ፍለጋ ወደ ሌላ አካባቢ በመሄድ ለወጪና እንግልት የሚዳረጉ ዜጎችን ችግር እንደሚቀርፍም ጠቁመዋል፡፡
በተመሳሳይ ባለሀብቱ በቡታጅራ ከተማ በ50 ሚሊየን ብር ያስገነቡት ሪዞርት ተመርቋል።
በጀማል ከዲሮ