Fana: At a Speed of Life!

የፋና ላምሮት የምዕራፍ 10 የፍጻሜ ተወዳዳሪዎች ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አራት የፋና ላምሮት የምዕራፍ 10 የስምንተኛው ሳምንት ተወዳዳሪዎች ለፍጻሜ ውድድር አለፉ፡፡

ተወዳዳሪዎቹ በሚቀጥለው ሳምንት በሚደረገው የፍጻሜ ውድድር አሸናፊ ለመሆን የሚፎካከሩ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከአንደኛ እስከ አራተኛ ለሚወጡት ድምጻውያን 500 ሺህ ብር ሽልማት ተዘጋጅቷል።

በሚቀጥለው ሳምንት ፍጻሜውን በሚያገኘው የፋና ላምሮት ውድድር ለአሸናፊ ተወዳዳሪ 200 ሺህ ብር፣ ሁለተኛ በመሆን ለሚያጠናቅቅ 150 ሺህ ብር፣ ሶስተኛ ለወጣው 100 ሺህ ብር እና አራተኛ ለወጣው 50 ሺህ ብር ሽልማት ይበረከትላቸዋል፡፡

ያለምወርቅ ጀምበሩ፣ ደሳለኝ አበበ፣ ገረመው ገብረጻዲቅ እና ዳንኤል አዱኛ በፍጻሜው የ500 ሺህ ብር ተካፋይ ተወዳዳሪዎች መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

የፍጻሜ ተወዳዳሪዎቹ 1 ሚሊየን ብር ወደሚያሸልመው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ማለፋቸውንም አረጋግጠዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.