የሀገር ውስጥ ዜና

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ14 ሰዎች ህይወት አለፈ

By Shambel Mihret

June 04, 2022

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ቀርሳ ወረዳ ከቀኑ 8፡30 አካባቢ የጭነት አይሱዙ ተሽከርካሪ ባደረሰው አደጋ የ14 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ማለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጐሹ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ፥ አደጋው የደረሰው ተሽከርካሪው ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ ሲሚንቶ ጭኖ እየተጓዘ ባለበት ወቅት ቀርሳ ከተማ ሲደርስ ፍሬን አልታዘዝ ብሎት ወደ ገበያ በመሄድ ላይ የነበሩ መንገደኞችን በመግጨቱ መሆኑንም ተናግረዋል።

በዚህም 8 ወንዶችና 6 ሴቶች ህይወታቸው አልፏል።

በአደጋው ህይወታቸው ካለፈው በተጨማሪ ሁለት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ለከፍተኛ ህክምና ወደ ድሬዳዋ ከተማ ተልከዋል።

የአደጋው መንስኤ ከፍጥነት ወሠን በላይ ማሽከርከርና ፍሬ ለመያዝ አለመቻል መሆኑንም ገልጸዋል።

ተሽከርካሪው በእግረኞች ላይ ጉዳት ካደረሰ በኋላ መገልበጡን የገለፁት ኢኒስፔክተር ቶሎሳ አሽከርካሪው ጉዳት ደርሶበት በቁጥጥር ስር መዋሉን ጠቁመዋል።

በተሾመ ኃይሉ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-