Fana: At a Speed of Life!

የፖሊስ አመራርና አባላት የምስጋናና የእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፖሊስ አመራርና አባላት የምስጋናና የእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው፡፡

በህግ ማስከበር ፣ በህልውና እና በህብረ ብሄራዊ አንድነት ዘመቻዎች ወቅት ጀግንነት ለፈፀሙና የላቀ የስራ ውጤት ላስመዘገቡ የፖሊስ አመራርና አባላት ነው የምስጋናና የእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብሩ “በመስዋዕትነታችን የሀገራችን አንድነትና የህዝባችን ሰላም ይረጋገጣል” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በመርሃ ግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣የኢትዮጵያ የፌዴራል ፖሊስ ሰራዊት ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ደመላሽ ገ/ሚካኤል፣ሚኒስትሮች፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

 

በአዳነች አበበ እና በለሊሴ ተስፋዬ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.