ዋልያዎቹ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በማላዊ ተሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከማላዊ ጋር የተጫወቱት ዋልያዎቹ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል፡፡
በማላዊ ቢንጉ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጋባዲኖ ማህዶ የማላዊን ሁለት ጎሎች በፍፁም ቅጣት ምት ሲያስቆጥር የኢትዮጵያን ብቸኛ ጎል አቡበከር ናስር በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡
ዋልያዎቹ ከዕረፍት መልስ የመሀል ክፍል ተጫዋቹን ጋቶች ፓኖም ወደ ሜዳ በማስገባት ጥሩ መንቀሳቀስ ቢችሉም÷ ያገኙትን የጎል አጋጣሚ ሳይጠቀሙ ቀርተዋል፡፡
የማላዊ ፕሬዚዳንት ዶክተር ላዛሩስ ቻክዌራ እና ምክትል ፕሬዚዳንቱ ዶክተር ሳውሎስ ቺሊማ የማላዊ ብሔራዊ ቡድንን በቢንጉ ብሔራዊ ስታዲየም ተገኝተው አበረታተዋል፡፡
በሚኪያስ አየለ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!