Fana: At a Speed of Life!

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የ2014 አፈጻጸም እየተገመገመ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2014 አፈጻጸም በአዋሽ እየተገመገመ ነው።

መድረኩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመሩት ሲሆን፥ የሁሉም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች 10 ወራት አፈጻጸም ቀርቧል።

የአፈጻጸም ሪፖርቱን የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ዶክተር ፍጹም አሰፋ አቅርበውታል።

በዚህ ወቅትም በዓመቱ ሀገሪቱ በውጫዊ እና ውስጣዊ ጫናዎች ውስጥ ብታልፍም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴው ሳይስተጓጎል ማስቀጠል ተችሏል ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

የበጋ ስንዴ፣ የሸቀጦች ወጪ ንግድ፣ ገቢ ምርትን በሀገር ውስጥ መተካት እንዲሁም የህዳሴ ግድብ ሀይል ማመንጨትን ጨምሮ በዓመቱ የተከናወኑ ስራዎች ትልቅ ፋይዳ እንደነበራቸው አመላክተዋል።

 

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.