ወጣቱን ኃይል ሊያሳጣን የሚችለውን ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ልንከላከለው ይገባል – ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አምራቹን የወጣት ኃይል ጉዳት ላይ ሊጥል የሚችለውን ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ለነገ ሳንል ልንከላከለው ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ ተናገሩ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በሰዎች የመነገድና በሕገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል የመከላከልና መቆጣጠር ምክር ቤት ዛሬ አንደኛ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው።
በጉባዔው ንግግር ያደረጉት የምክር ቤቱ ሰብሳቢና የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ወጣቱን ኃይል ሊያሳጣን የሚችለውን ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ለነገ ሳንል ልንከላከለው ይገባል ብለዋል።
ወንጀሉን መከላከልና መቆጣጠር እንዲቻልና በዚህ ድርጊት የሚሳተፉትንም በህግ ተጠያቂ ማድረግ የሚያስችለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሰዎች የመነገድ እና በህገ ወጥ መንገድ ሰዎችን ድንበር የማሻገር ወንጀል የመከላከልና መቆጣጠር ምክር ቤት እና የትብብር ጥምረት ደንብ በአዋጅ ቁጥር 126/2014 ግንቦት4 መጽደቁ ይታወሳል።
የዚህ ምክር ቤት ዋና ዓላማም ይሄንን ህገወጥ ወንጀል ቀድሞ ለመከላከልና በወንጀሉ የተጎዱትንም መልሶ ለማቋቋም የባለድርሻ አካላትን ርብርብ የሚያጠናክር መሆኑ ተጠቁሟል።
በይስማው አደራው
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!