Fana: At a Speed of Life!

በግለሰብ ቤት የሞርታር ተተኳሽ ተደብቆ ተገኘ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ ልዩ ስሙ 02 ቀበሌ ጢሳ አባሊማ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በግለሰብ መፀዳጃ ቤት ውስጥ 23 የሞርታር ተተኳሽ መገኘቱን የአምባሰል ወረዳ ሚሊሻ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ተተኳሾ ከኀብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት በተደረገ ፍተሻ መገኘቱንም ነው የገለጸው።

የተገኘው የሞርታር ተተኳሽ አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን ከአካባቢው ሽሽቶ ሲሄድ ጥሎት የሄደ ሊሆን እንደሚችል የሚገመት ሲሆን፥ ተተኳሹ የተገኘበት ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

መረጃው የአምባሰል ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.