Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያና ብሪታንያ ባለሀብቶች በጋራ ለመስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያና ብሪታንያ ባለሀብቶች በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሔደ፡፡

የእንግሊዝ ኤምባሲ ያዘጋጀው ይሄው ውይይት፥ የንግዱን ማህበረሰብ ማቀራረብና አብረው መስራት የሚችሉባቸው ሁኔታዎችን መፍጠር ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያና አፍሪካ ህብረት የብሪታንያ አምባሳደር አላስተር መክፌል፥ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት መሰረት በማድረግ ግንኙነቶችን ማጠናከር እጅግ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

እያደገ ያለውን የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለመደገፍ ብሎም አብሮ ለመስራት የብሪታንያ መንግስትና ኩባንያዎች ዝግጁ መሆናቸውንም ነው አምባሳደሩ የገለጹት።

ሀገር-በቀል ኩባንያዎችን ለማበረታታትም ቁርጠኛ መሆናቸውን አንስተዋል።

ከውይይቱ በተለይ በንግዱ ዘርፍ የኢትዮጵያ ኩባንያዎች ያሉባቸውን የአቅም ችግሮች ለመፍታት የሽርክና ንግድን ጨምሮ አብሮ መስራት እና በብሪታንያ የገበያ አማራጮች የሚያገኙባቸውን እድሎች ለማመቻቸትና ውጤት ለማምጣት ጥረት እንደሚደረግም ተጠቁሟል።

በውይይቱ ረዥም ዓመታትን በንግድ ስራ ዘርፍ ያሳለፉ ኩባንያዎች መሳተፋቸው ታውቋል።

በሀብታሙ ተ/ስላሴ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.