የሀገር ውስጥ ዜና

ድርጅቱ በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

By Shambel Mihret

June 07, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል በፈጸመው ወረራ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል የ5 ሚሊየን በር ድጋፍ አድርጓል።በተጨማሪም ድርጅቱ የሁለት ሚሊየን ብር የዓይነት ድጋፍ ያደረገ ሲሆን÷ድጋፉን የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሮባ መገርሳ ለአፋር ክልል ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ መሐመድ አስረክበዋል። ድርጅቱ ለክልሉ ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የአፋር ክልል የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ÷ ሁሉም አገር ወዳድ ዜጋና ተቋማት በክልሉ በጦርነት ለተጎዱ ወገኖች ከዕለት ደራሽ ሰብዓዊ እርዳታ ጀምሮ እስከ መልሶ ማቋቋም እየተከናወኑ ላሉ ስራዎች ድጋፍ ማድረጉን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። አሸባሪው ሕወሓት በአፋር ክልል በፈጸመው ወረራ ምክንያት 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ዜጎች የዕለት ደራሽ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ኢዜአ ዘግቧል፡፡