Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ለ6 ሺህ 23 ኢንተርፕራይዞችና አንቀሳቃሾች የመስሪያ ቦታ ለማስተላለፍ ተችሏል- አቶ ጃንጥራር አባይ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት 10 ወራት ለ6 ሺህ 23 ኢንተርፕራይዞችና አንቀሳቃሾች የመስሪያ ቦታ ማስተላለፍ መቻሉ ተገልጿል፡፡
 
በምክትል ከንቲባና የሥራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ÷በህገ ወጥ ወንገድ ተይዘው የነበሩ ሼዶችን በማስመለስ፣በማሸጋሸግና አዳዲስ በመገንባት 63 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ የመስሪያ ቦታዎችን ለኢንተርፕራይዞችና አንቀሳቃሾች ማስተላለፍ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
 
አቶ ጃንጥራር በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በብልሹ አሰራሮችና በሌብነት መታገያ ንቅናቄ ዕቅድ አፈፃፀም ላይ እንዳሉት ÷ ቢሮው ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ይነሱ የነበሩ ችግሮችንና ቅሬታዎችን በጥናት ተመስርቶ በመለየት ለመፍታት ባደረገው ጥረት ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡
 
ባለፉት10 ወራትም ቢሮው 63 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ ስፋት ያላቸውን የመስሪያ ቦታዎችን በህገ ወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ በማስመለስ፣ አዳዲስ በመገንባትና የማሻሻያ ስራዎችን በማከናወን ለ1ሺህ 375 ኢንተርፕራይዞች እና ለ4ሺህ 648 አንቀሳቃሾች ለማስተላለፍ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡
 
ከሚመለከታቸው ህግ አስከባሪ የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀትም በ 2 ሺህ 311 ህገ ወጥ ኢንተርፕራይዞች ላይ እርምጃ መውሰድ መቻሉንም ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.