ስፓርት

በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን የወርቅና የብር ሜዳልያዎች አገኘች

By Mikias Ayele

June 08, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን የወርቅና የብር ሜዳልያዎች አገኘች።

ሜዳልያዎቹ በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች የተገኘ ነው።

በውድድሩ አትሌት ሞገስ ጥኡማይ እና አትሌት ጭምዴሳ ደበላ ተከታትለው በመግባት ለሃገራቸው ሜዳልያዎቹን ማስገኘታቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደራሽን መረጃ ያመላክታል።