Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ አፍሪካ የጥበባትና ባህል ፌስቲቫል በመጪው ማሰኞ በይፋ ይከፈታል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የጥበባትና ባህል ፌስቲቫል በመጪው ማክሰኞ በይፋ እንደሚጀመር የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋራ ባዘጋጁት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቀዋል፡፡
የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጀላ መርዳሳ እንደተናገሩት በፌስቲቫሉ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ 13 የአፍሪካ ሃገራት የሚሳተፉ ሲሆን በመርሃግበሩ ላይ አገራቱን የሚያስተዋዉቁ ዝግጅቶች ይቀርባሉ፡፡
ፌስቲቫሉ በዋናነት ተሳታፊ አገራትን ለዓለም የሚያስተዋውቁ ዐውደ ጥናቶች፣ ዐውደ ርዕዮች፣ ኪነ ጥበባዊ እና ስፖርታዊ ዝግጅቶች እንደሚቀርቡ ሚኒስትሩ አቶ ቀጀላ መርዳሳ አስረድተዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በበኩላቸው ፌስቲቫሉ የምስራቅ አፍሪካ ሃገራትን በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፎች በተለይም በባህል፣ በንግድና ኢንቨስትመንት መስኮች ለማስተሳሰር የጎላ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ተናግረዋል፡፡
በወንደሰን አረጋኸኝ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.