የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ ትናንት የጣለው ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ አንድ ተማሪ መውሰዱ ተነገረ

By Alemayehu Geremew

June 09, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ትናንት በጣለው ዝናብ አንድ ተማሪ በጎርፍ እንደተወሰደ ተነገረ።

ተማሪው በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ላዛሪስት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት ተማሪ መሆኑም ነው የተመለከተው፡፡

ተማሪው በጎርፍ የተወሰደው በትናንትናው ዕለት ዘጠኝ ሠዓት አካባቢ በጣለው ዝናብ መሆኑን የአዲስ አባባ እሳትና ድንገተኛ አደጋ የኮሙኒኬሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ ንጋቱ ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በጎርፉ የተወሰደው ተማሪ በትምህርት መውጫ ሠዓት ላይ ከትንሽ ወንድሙ ጋር ወደ ቤት እየሄዱ እንደነበርም ተገልጿል፡፡

እስከዛሬ ጠዋት የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ሠራተኞቹ ከኅብረተስቡ ጋር በመሆን ተማሪውን የመፈለጉን ሥራ ቀጥለዋል ተብሏል፡፡

ወላጆች በክረምቱ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ሲልኩም ሆነ ሲቀበሉ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉላቸው የእሳትና ድንገተኛ አደጋ በመልዕክቱ አሳስቧል፡፡

በሲሳይ ጌትነት