Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ 169 ኢንተርፕራይዞች ወደ መካከለኛ ደረጃ ኢንተርፕራይዝነት ተሸጋገሩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 169 ኢንተርፕራይዞችን ወደ መካከለኛ ደረጃ ኢንተርፕራይዝ አሸጋገረ፡፡

11ኛው ዙር የኢንተርፕራይዝ ሽግግር ምረቃ መርሀ ግብር ዛሬ በኢሊሊ ሆቴል እየተካሄደ ነው ፡፡

የምረቃ መርሃ ግብሩ “የኢንተርፕራይዝ ሽግግር ለኢንዱስትሪ መሰረት” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ ያለው፡፡

በመርሃግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤና ምክትል ከንቲባና የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሀላፊ አቶ ዣንጥራር አባይን ጨምሮ ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል::

በአጠቃላይ 1 ሺህ 625 ኢንተርፕራይዞች መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ደረጃ ላይ የሚገኙ ናቸው ተብሏል::

በዘቢብ ተክላይ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.