Fana: At a Speed of Life!

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች ከጋምቤላ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች ከጋምቤላ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር የትውውቅ እና የውይይት መድረክ አካሂደዋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ÷ መሠረታዊ በሆኑ አገራዊ ጉዳዩች ላይ የሚታየውን ስር የሰደዱ የሃሳብ ልዩነቶች እና አለመግባባቶች ለመፍታት ሰፋፊ አገራዊ የሕዝብ ምክክሮችን አካታች በሆነ መንገድ ማስኬድ እንዲቻል መደረጉ ተገቢ ነው ብለዋል።

በውጤቱም ለዜጎች የምትመች፣ ለጎረቤት አገራትም የሰላም እና ብልፅግና ተምሳሌት የሆነች ጠንካራ ኢትዮጵያን ለመገንባት እንደሚያስችል ነው የተናገሩት።

እንደ አገር ካሳለፍናቸው ፈተናዎች ይበልጥ ወደ ፊት የሚቀሩን ይበልጣሉ እና በፈተና ላለመውደቅ ልዩነታችንን በማጥበብ አንድነታችንን ማጠናከር ይገባል ሲሉም አስረድተዋል።

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ተገኘወርቅ ጌቱ በበኩላቸው ÷ እስካሁን መግባባት ላይ ያልተደረሱባቸው እና የኢትዮጵያን ህልውና የሚፈታተኑ የተለያዩ ቸአገራዊ ጉዳዮች መኖራቸውን አንስተዋል፡፡

አገራዊ ምክክሩ እነዚህን ችግሮች በመፍታት ለመጪው ትውልድ ሰላማዊ አገር ለማስረከብ እንደሚያስችልም አብራርተዋል።

በክልሉ ያሉትን የተፈጥሮ ሃብቶች ማልማት ከተቻለ የተፈለገውን ሰላም እና ዕድገት ማረጋገጥ እንደሚቻል በውይይት መድረኩ ተመላክቷል።

ከዚህ ባለፈም በመድረኩ ስለ ኮሚሽኑ አላማ ተልዕኮ እና ዕራይ ማብራሪያ መሰጠቱን ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.