1ሺህ 169 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ አገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ ችግር ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 169 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ተመላሾቹም በሙሉ ወንዶች መሆናቸውን ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉ ተገልጿል፡፡ እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው ከ 35ሺህ 497 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ተጠቁሟል፡፡