Fana: At a Speed of Life!

በሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ በግልጽ ተነጋግሮ መግባባት መፍጠር የህልውና ጉዳይ ነው-አቶ ታዬ ደንደአ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ በግልጽ ተነጋግሮ መግባባት መፍጠር የህልውና ጉዳይ ነው ሲሉ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ታዬ ደንደአ ተናገሩ፡፡

አካታች ብሄራዊ ምክክር ለብሄራዊ መግባባታችን፣ ለዘላቂ ሰላማችንና ለአብሮነታችን በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተካሄዷል፡፡

በውይይት መድረኩ ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስትር ዴኤታው ታዬ ደንደአ እንደ ሀገር ባጋጠሙን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ላይ በመምከር ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር በቅን ልቦና ላይ የተመሰረተ ውይይት ማድረግ ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለም ብለዋል።

ልዩነቶችን በአግባቡ በማስተናገድ በዋና ዋና ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ በግልጽ ተነጋግሮ መግባባት መፍጠር የህልውና ጉዳይ ነው ሲሉም አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡

ምክክራችን ውድቀታችንን ወደ ከፍታ መቀየር አለበት ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ልዩነቶችን በአግባቡ በማስተናገድ በዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ በመወያየትና በመግባባት ጠንካራ ሀገር መገንባት ከሁላችን ይጠበቃልም ብለዋል።

የሁሉን የነቃ ተሳትፎ በሚጠይቀው አካታች ብሄራዊ የምክክር መድረክ ሁሉም ዜጋ በቅንነት እና በቁርጠኝነት ተሳትፎ ሊያደርግ ይገባልማለታቸውን ከወለይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.