Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያ ጦር የዩክሬንን ትልቅ የጦር መጋዘን ማውደሙ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ጦር የምዕራባውያን የጦር መሳሪያዎች ይገኙበታል የተባለን የዩክሬን ትልቅ የጦር መሳሪያ መጋዘን ማውደሙ ተሰማ ፡፡

ኢንተርፋክስ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴርን ጠቅሶ እንደዘገበው የሩሲያ ሀይሎች በዩክሬን ተርኖፒል ክልል የሚገኘውን የአሜሪካ እና የአውሮፓ ጦር መሳሪያ ይገኝበታል የተባለ መጋዘን በካሊብር ሚሳኤል አውድመዋል፡፡

በተጨማሪም ሶስት የዩክሬን ሱ 25 ተዋጊ ጄቶች ዶኔስክ አቅራቢያ መተው መጣላቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል ሲል ቲ አር ቲ ዘግቧል፡፡

109ኛ ቀኑን የያዘውን የሩሲያ እና የዩክሬን ጦርነት ተጽዕኖ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ መታየት መጀመሩን መረጃዎች ያመላክታሉ።

በሀገራቱ መካከል የሰላም ድርድር ጥረቶች ሲደረጉ ቢቆይም የሚታይ ውጤት ማምጣት እንዳልተቻለም ዘገባዎች ያስረዳሉ፡፡

ምዕራባዊያን ሀገራት ለዩክሬን የሚያደርጉትን የጦር መሳሪያ ድጋፍ አጠናክረው መቀጠላቸው ደግሞ ጦርነቱን ይበልጥ አባብሶታል በሚል አንዳንድ ሀገራት ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.