ስፓርት

ኢትዮጵያ በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 5ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች

By Feven Bishaw

June 12, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 5ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች።

በውድድሩ ኢትዮጵያ በ4 ወርቅ፣ 6 ብር እና 4 ነሃስ በአጠቃላይ በ14 ሜዳልያ 5ኛ ደረጃ ይዛ ማጠናቀቋን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል።

በውድድሩ የመጨረሻ ቀን በሴቶች 3 ሺህ መሰናክል እና በ5 ሺህ ወንዶች ውድድር ሁለት የወርቅ ሜዳልያዎችን ማግኘት ችላለች።

ከዚህ ባለፈም 2 የብር እና 1 የነሐስ ሜዳልያም በማጠናቀቂያው ቀን በሴቶች 3 ሺህ መሰናክል እና በእርምጃ ውድድር ማግኘቷ ይታወቃል።