የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሉሲዎቹ እና ለአዲስ አበባ ከተማ ልዑካን የ5 ሚሊየን ብር ሽልማት አበረከተ

By Feven Bishaw

June 12, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሴቶች ብሄራዊ ቡድን እንዲሁም በአንደኛው ሃገር አቀፍ የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሊምፒክ ለተሳተፈው ለአዲስ አበባ ከተማ ልዑካን ቡድን ለእያንዳንዳቸው የ5 ሚሊየን ብር ሽልማት አበርክቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አበቤ በዛሬው ዕለት በአንደኛው ሀገር አቀፍ ወጣቶች ኦሊምፒክ ውድድር ላይ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የአዲስ አበባ የልዑካን ቡድን እና በሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ላይ ሦስተኛ ደረጃ በመያዝ ላጠናቀቁት የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) የ5 ሚሊየን ብር ሽልማት አበርክተዋል፡፡