የሀገር ውስጥ ዜና

በኩዌት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው የሚያደርጉትን ድጋፍ ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ

By Alemayehu Geremew

June 13, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኩዌት የኢትዮጵያ አምባሳደር ሐሰን ታጁ በሀገሪቷ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለሃገራቸው የሚያደርጉትን ድጋፍ ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ላይ ተወያዩ፡፡

አምባሳደሩ በቀጣይ ማኅበረሰቡን በሚያስፈልገው ሁሉ ለመደገፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

በኩዌት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲቀጥሉና መብታቸውን ለማስከበር ከኤምባሲው ጋር በቅርበት እንዲሠሩም ጠይቀዋል።

ከውይይቱ በኋላ በኩዌት ሆስፒታል በመገኘት የሚገኙ ታካሚ ኢትዮጵያውንን መጎብኘታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡