Fana: At a Speed of Life!

ሦስተኛው የኢትዮ-ናይጄሪያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ በናይጄሪያ ያደረጉኑትን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ተከትሎ ሦስተኛው የኢትዮ -ናይጄሪያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

የጋራ ኮሚሽን ስብሰባው ከሁለት ሳምንት በፊት የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በናይጄሪያ ያደረጉኑትን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ተከትሎ መካሄዱ ነው የተገለጸው።

በስብሰባው ላይ ሀገራቱ የተስማሙባቸውን የሁለትዮሽ ስምምነቶች እና ሊሰሩባቸው በሚችሉ ሀብቶቻቸው ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

አዲስ አበባ እና አቡጃ ቀደም ሲል በአየር፣ ንግድ፣ ባህል፣ ሳይንስ፣ ትምህርት ፣ ባህልና ቱሪዝም ዘርፎች እንዲሁም በግብርናው መስክ በጋራ ለመስራት የትብብር ስምምነት ፈጽመው እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ተገልጿል።

ዛሬ በአዲስ አበባ ውስጥ እየተካሄደ በሚገኘው የሁለቱ ሀገራት የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ፥ ቀደም ሲል በማዕድን እና ኢንዱስትሪ ዘርፎችም ላይ በጋራ ለመስራት የተስሟሙባቸውን ጉዳዮችች ጨምሮ አብሮ መስራት የሚችሉባቸው ሌሎች ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በፀጋዬ ወንድወሰን

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.