ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ነገ ከፓርላማው ለሚነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ ይሰጣሉ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች 6ኛው ምክር ቤት በ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ነገ በሚያካሂደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቃል የሚሰጡትን ምላሽ ያዳምጣል።
ነገ ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በሚካሄደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ፥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በተያዘው አጀንዳ መሠረትም፥ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ጥያቄዎችን ያቀርባሉ፤ እንደዚሁም አስተያየቶችን ይሰጣሉ።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!