አቶ ደመቀ መኮንን ከጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መከሩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊዊጂ ዲ ማዮ ጋር በሁለትዮሽና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ።
አቶ ደመቀ በዚህ ወቅት ከጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት፣ በቀጠናዊ ጉዳዮችና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ምክክር ማካሄዳቸውን ገልጸዋል፡፡
የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ መሆኑን ጠቅሰው የጣሊያን መንግሥት ፥ በኢትዮጵያ የነበረው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ሚዛናዊነት በማሳየቱ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የሁለቱን ሀገራት የጋራ ጥቅም በሚያረጋግጥ መልኩ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውንም አቶ ደመቀ መኮንን ጠቁመዋል።
የጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን ፥ በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉብኝት ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ኬንያ እንደሚያቀኑ የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ጣሊያን ከአፍሪካ አገራት ጋር ያላትን ትብብር ማጠናከር ዓላማ ያደረገ መሆኑንም ኢዜአ ዘግቧል።
ሚኒስትሩ ቀደም ብለው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁ ከኢጋድ ዋና ፀሃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበዬሁ ጋር መወያየታቸው የሚታወስ ነው።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!