የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢትዮጵያዊ ሁሉ ክልሉን እንዲደግፍ ጥሪ አቀረቡ
አዲስ አበባ፣ሰኔ 6፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለክልሉ እስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ፡፡
ርዕሰ መስተዳደሩ የክልሉ መንግስት ክልሉን ለማጠናከር የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ሰኔ 15 በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል እንደሚካሄድ ጠቁመዋል።
በዚህ መርሃ ግብርም ሆነ በሌሎች ቦታዎች በሚኖሩ ዝግጅቶች ሁሉም ኢትዮጵያዊ አቅሙ በፈቀደ መጠን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
ለኢንቨስትመንት ምቹ በሆነው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል አልሚ ባለሀብቶች መዋዕለ ንዋያቸውን በክልሉ በማልማት ስኬታማ መሆን እንደሚችሉ ርዕሰ መስተዳደሩ ገልፀዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳደሩ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ክልሉን በመደገፍ ወንድማማችነትን እንዲያጠናክሩ ጥሪ ማቅረባቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ዘገባ ያመላክታል፡