Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የመንግሥት ሠራተኞችን የኑሮ ውድነት ጫና ለማቃለል 6 ነጥብ 8 ሚሊየን ሊትር ዘይት ሊሰራጭ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ሠራተኞችን የኑሮ ውድነት ጫና ለማቃለል 6 ሚሊየን 807 ሺህ ሊትር ዘይት እና 3 ሺህ 500 ኩንታል ስኳር በተያዘው ሰኔ ወር ስርጭት ለማካሄድ መታቀዱን የከተማዋ የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታውቋል፡፡
በቢሮው የግብይት ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ ደመቀ ሰይፈ እንደገለጹት÷ የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ንቅናቄን በማቀድና በቢሮው ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን በመለየት ለመፍታት ጥረት በማድረግ ላይ ነው፡፡
በዚህም በመንግሥት ሠራተኞች ከመሰረታዊ ሸቀጦች አቅርቦት ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ነው ያብራሩት፡፡
ከዚህ አኳያም ቢሮው በያዝነው ወር በፌዴራል፣ በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ ልዩ ዞን ለሚገኙ የተቋም ሠራተኞች 580 ሺህ አንዲሁም ለክፍለ ከተሞች 6 ሚሊየን 227 ሺህ በድምሩ 6 ሚሊየን 807 ሺህ ሊትር የምግብ ዘይት ለማሰራጨት አቅዷል ነው ያሉት።
ከዚህ ባለፈም 3ሺህ 500 ኩንታል ስኳር የሚሰራጭ መሆኑና የአንድ ኪሎ ስኳር ዋጋም 42 ብር ከ16 ሳንቲም እንደሆነ መጠቆማቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ቢሮው በአሁኑ ወቅት ለመንግሥት ሠራተኞች የሚያካሂደው የመሰረታዊ ሸቀጦች አቅርቦት በቴክኖለጂ በመታገዝ ስርጭቱን ለማቀላጠፍና ውጣ ውረዶችን ለመቀነስ ጥረት እያደረገ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.