Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሩ ውጤታማ እንዲሆን አመራሩ በቁርጠኝነት እንዲሰራ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ውጤታማነት አመራሩ በቁርጠኝነት እንዲረባረብ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ጥሪ አቀረቡ፡፡

በክልሉ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ውጤታማ ለማድረግ የተቋቋመው ግብረሃይል የአረንጓዴ አሻራውን የተሳካ ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክሯል።

በመድረኩም  የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ÷በክልሉ በዘንድሮው አመት ለሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ አሳስበዋል።

በተጨማሪም አመራሩ የአቅመ ደካማ ወገኖች ቤት የማደስ እና ማዕድ የማጋራት ስራ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ነው ያሉት፡፡

ይህም በተለይም የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ እና በአሁኑ ወቅት እየተስተዋለ የሚገኘውን የኑሮ ውድነት ጫና ከመቀነስ አንፃር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል።

ችግኝ ከመትከል ባለፈም መንከባከብና እንዲፀድቅ ማድረግ ያስፈልጋል ለዚህም የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

በክልሉ በዘንድሮው ከሚተከሉ ችግኞች መካከል 70 በመቶው ለምግብነት የሚውሉ የተለያዩ ፍራፍሬዎችና አትክልቶች መሆናቸውን ከሐረሪ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.