የአዕምሯዊ ንብረት ሀገራዊና የሴክተር የልማት ግቦችን ከማሳካት አንጻር ቁልፍ ሚና እንዳለው ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዕምሯዊ ንብረት ሀገራዊና የሴክተር የልማት ግቦችን ከማሳካት አንጻር ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤርሚያስ የማነ ብርሃን÷ባለስልጣኑ ከዓለም አዕምሯዊ ንብረት ድርጅት ጋር በመሆን ሀገራዊ የአዕምሯዊ ንብረት ፖሊሲ ማዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡
አዕምሯዊ ንብረት ሀገራዊና የሴክተር የልማት ግቦችን ከማሳካት አንጻር ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመው፥ በተጨማሪም ማህበራዊ፣ ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ግቦችን ለማበረታታትና ለማሳካት ወጥ የሆነ የፖሊሲ አቅጣጫ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
የአዕምሯዊ ንብረት ድርጅት ተወካይ ሎሪታ አሴይዱ ሀገራዊ የአዕምሯዊ ንብረት ፖሊሲ መንግስት የአዕምሯዊ ንብረት ስርዓቱን እንደ ልማት መሳሪያ እንዲጠቀም የሚያበረታታ እና የአዕምሯዊ ንብረት እሴቶችን ማመንጨት፣ ማስጠበቅ እና ለገበያ ማዋልን ያፋጥናል ነው ያሉት፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!