Fana: At a Speed of Life!

የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ የፍትህ እና ዴሞክራሲ ቋሚ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 8፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሰዓዳ አብዱረህማን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ፣ የፍትህ እና ዴሞክራሲ ቋሚ ኮሚቴ ጋር መንግስት ሕግ ለማስከበር እየወሰደ ባለው እርምጃ ዙሪያ ተወያዩ፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በክልሉ አንዳንድ ዞኖች፥ ወረዳዎችና ከተሞች ምልከታ እንደሚያደርግም ተገልጿል፡፡

በምልከታው ዙሪያ ከጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሰዓዳ አብዱረህማን ጋር የክልሉ መንግስት ሕግ ለማስከበር እየወሰደ ባለው ርምጃ ዙሪያ መምከሩንም ከጨፌው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮለኔል አበበ ገረሱ አጠቃላይ የክልሉን ፀጥታ ለማስከበር መንግስት እየወሰደ ያለውን ርምጃና ሕዝቡ ለፀጥታ አካላት እያደረገ ባለው ድጋፍ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.