በሶማሌ ክልል በአዩን ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ሰኔ 8፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ኖጎብ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
አደጋው በክልሉ ኖጎብ ዞን አይን ወረዳ ዳሪዳ ቀበሌ ባለ ሁለት ጋቢና ቶዮታ መኪና የኋላ ጎማ ወልቆ በመውደቁ የደረሰ ነው።
በአደጋው የአራት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት እንደደረሰ ከሶማሌ ከልል መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡