Fana: At a Speed of Life!

የግብርናውን ዘርፍ ዲጂታል በማድረግ የአርሶ አደደሩን ብልጽግና ማረጋገጥ ይገባል- አቶ ዑመር ሁሴን

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ዓመታት ቴሌኮምን ጨምሮ በተለያዩ ተቋማት የታየው የዲጂታል ኢኮኖሚ ተስፋ ሰጭ በመሆኑ የግብርናውን ዘርፍም ዲጂታል በማድረግ ለኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ብልፅግናን ለማምጣት መሰራት አለበት ሲሉ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን ተናገሩ፡፡
በ2030 የኢትዮጵያ ዲጂታል ግብርና ኤክስቴንሽን የምክር አገልግሎት ፍኖተ ካርታ ላይ ውይይት በመካሄድ ላይ ነው፡፡
በመድረኩ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተሳታፊዎች እና የልማት አጋሮች ተገኝተዋል።
የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የዲጂታል ቴክኖሎጂን አስፈላጊነት ልክ እንደሞተር አጽንኦት ልንሰጠው ይገባል ብለዋል።
የገበሬዎች ልማት እና ብልጽግናን ለማሳደግ “ዲጂታል ግብርና” ለሕዝቡ እኩል የመረጃ ተደራሽነት እድልን ለመስጠት የተሻለ መንገድ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡
በ2030 የሀገሪቱን የግብርና ምርት በእጥፍ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ጠቁመው÷ ይህ የዲጂታል ግብርና ቴክኖሎጂ አርሶ አደሩ የማምረት አቅሙን ለማሳደግ ያግዛል ብለዋል፡፡
የዲጂታል ግብርና ፍኖተ ካርታ ዓላማ መረጃን ተደራሽ በማድረግ አርሶ አደሮችን ማብቃት እና ማስቻልን ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ባለፉት ዓመታት ቴሌኮምን ጨምሮ በተለያዩ ተቋማት የታየው የዲጂታል ኢኮኖሚ ተስፋ ሰጭ መሆኑና የግብርናውን ዘርፍ ዲጂታል በማድረግም ለኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ብልፅግናን ለማምጣት መሰራት እንዳለበትም ተመላክቷል።
በይስማው አደራው
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.