Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ስለሺ በቀለ ከአምባሳደር ቲቦር ናዥ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶክተር ስለሺ በቀለ ከቀድሞው የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ቲቦር ናዥ እና ከቴክሳስ የቴክኖሎጂ እና አንግሎ ስቴት ዩኒቨርሲቲዎች 15 ተማሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዚህ ወቅት ስለ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ታሪካዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት ገለጻ አድርገውላቸዋል።

በስነ ስርአቱ ላይ ተማሪዎቹ የኢትዮጵያን ባሕላዊ የቡና አፈላል ሥነ-ሥርዓት በመታደም የኢትዮጵያን ምግቦች መመገባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ተማሪዎቹ በሥነ-ሥርዓቶቹ ላይ መታደማቸው ስለ ኢትዮጵያን እንዲያውቁ እና የሁለቱን ሀገራት ባሕል ፣ ዕሴት እና ግንኙነት እንዲረዱ እና ለሌሎችም እንዲያስተዋውቁ እንደሚያግዝም ነው የተገለጸው።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.