Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2021 ከአፍሪካ አምሥት የውጭ ቀጥተኛ የኢንቨስትመንት መዳረሻዎች አንዷ መሆኗ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የንግድና ልማት ኮንፈረንስ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2021 ከአፍሪካ ሀገራት አምሥት የውጭ ቀጥተኛ የኢንቨስትመንት መዳረሻዎች መካከል አንዷ መሆኗን አስታወቀ።

በሀገራት ንግድ እና ዕድገት ላይ በተዘጋጀው ኮንፈረንስ ላይ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ አምሥት የ2021 የውጭ ቀጥተኛ የኢንቨስትመንት መዳረሻዎች ውስጥ አንዷ መሆኗን አሁናዊ ዓለም አቀፋዊ የኢንቨስትመንት ሪፖርቱን መሠረት አድርጎ አመላክቷል፡፡

ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2021 በውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት 4 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር እንዳንቀሳቀሰች እና ይህም ከ2020 አንጻር የ79 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመረጃው ያመላከተው፡፡

የኢትዮጵያ የ2021 የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በዓመቱ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት በጠቅላላ ካካሄዱት ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት በግማሽ እንደሚልቅም ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.