በአዲስ አበባ 7ኛው ከተማ አቀፍ የሳይንስና የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ያዘጋጀው 7ኛው ከተማ አቀፍ የሳይንስ ፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ወዳጅነት ፓርክ እየተካሄደ ነው።
የሳይንስና የፈጠራ ስራ አውደ ርዕዩ “የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ የብልጽግና ጉዛችንን በሳይንስና ፈጠራ ዕውን እናደርጋለን!” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
ከሰኔ 9 ቀን እስከ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ የሚካሄደው አውደ ርዕይ፥ በተማሪዎች መካከል ጤናማ ውድድርን በመፍጠር የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እንደሚረዳ ተገልጿል።
በመርሐ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አበቤን ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራል እና የከተማ አስተዳደሩ የስራ ሃላፊዎች ፣ ተማሪዎች ፣ መምህራን ፣ የትምህርት ባለሙያዎች እና አመራሮች መሳተፋቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!