ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ጅማ አባ ጅፋር እና ፋሲል ከነማ ድል ቀንቷቸዋል

By Mikias Ayele

June 16, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ26ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጅማ አባ ጅፋር ሃድያ ሆሳዕናን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ረፋድ ላይ በተደረገው ጨዋታ አንጋፋው ዳዊት እስጢፋኖስ ከረጅም ጊዜ በኋላ ባስቆጠራት ጎል ጅማ አባ ጅፋር ሙሉ ሶስት ነጥብ ማግኘት ችሏል፡፡

በ23 ነጥብ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው ጅማ አባ ጅፋር የዛሬው ድል ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት ለሚያደርገው ጥረት ከፍተኛ መነቃቃትን ፈጥሮለታል፡፡

10 ሰአት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ደግሞ ፋሲል ከነማ ሰበታ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በያሬድ ባየህ ጎል አሸናፊ የሆነው ፋሲል ከመሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 3 ዝቅ ማድረግ ችሏል።