ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ከአውሮፓ ህብረት ልማት ትብብር የስራ ሃላፊ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍትህ ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዮስ ከአውሮፓ ህብረት የልማት ትብብር የስራ ሃላፊ ፌራን ሚሪያም ጋር በብራሰልስ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ በሚዳረስበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ኢትዮጵያ በግጭቱ ወቅት ተፈጽመዋል በተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ተጠያቂነትን ለማስፈን በወሰደቻቸው እርምጃዎች ዙሪያ መወያየታቸው ተመላክቷል፡፡
ፌራን ሚሪያም አሁን ላይ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ተከስቶ የነበረው ግጭት መሻሻል እንዳሳየ መገንዘባቸውን አንስተው÷ ለዚህም አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡
በአፍሪካ ህብረት መሪነት እየካሄደ ባለው የድርድር ሂደትም ዘላቂ ሰላም እንደሚሰፍን እምነታቸው እንደሆነ መግለጻቸውን በብራሰል ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!