ግብፅ በኢትዮጵያ ከገጠማት መራር ሽንፈት በኋላ አሰልጣኟን አሰናበተች
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብፅ እግር ኳስ ማህበር የብሄራዊ ቡድኑን አሰልጣኝ ኢሀብ ጋላልን ከአሰልጣኝነት አሰናበተ።
ግብጽ የዛሬ ሳምንት ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ ጨዋታዋን በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከጨዋታ ብልጫ ጋር 2 ለ 0 መሸነፏ ይታወሳል።
ከዚህ ባለፈም በወዳጅነት ጨዋታ ከትናንት በስትያ በደቡብ ኮሪያ የ4 ለ 1 ሽንፈት አስተናግዳለች።
ከደቂቃዎች በፊት ይፋ በሆነው መረጃ መሰረት ደግሞ የሀገሪቱ የእግር ኳስ ማኅበር የብሔራዊ ቡድኑን አሠልጣኝ ከመንበሩ ማንሳቱን ይጠቁማል።
የ54 ዓመቱ አሠልጣኝ ቡድኑን ከተረከቡ 2 ወር ያልሞላቸው ቢሆንም በኢትዮጵያ የደረሰባቸው ሽንፈት መንበራቸው እንዲንገጫገጭ ማድረጉን ሶከር ኢትዮጵያ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።