Fana: At a Speed of Life!

የሳንሱሲ- ታጠቅ -ኬላ የመንገድ ግንባታ ስራ ሙሉ በሙሉ ለትራፊክ ክፍት ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳንሱሲ- ታጠቅ -ኬላ የመንገድ ግንባታ ስራ ሙሉ በሙሉ ለትራፊክ ክፍት ተደረገ፡፡

የመገናኛ ብዙሃን የሳንሱሲ- ታጠቅ -ኬላ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ስራ አፈጻጸም ሂደትን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱም የመንገዱ የግንባታ አፈፃፀም 97 ነጥብ 3 በመቶ መድረሱ እና የአስፋልት ንጣፍ ስራው ተጠናቆ በሙሉ አቅም ለትራፊክ ክፍት መደረጉ ተገልጿል፡፡

የግንባታው አካል የሆነው የእግረኛ መንገድ፣ የትራፊክ ምልክት ተከላ ስራን ጨምሮ ጥቃቅን ስራዎችም በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

የሳንሱሲ- ታጠቅ – ኬላ 13 ነጥብ 54 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ÷መንገዱ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ ነው የተገነባው።

ለግንባታው 825 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን ÷ ወጪው የተሸፈነውም ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት ነው ተብሏል፡፡

መንገዱ ወደ አምቦ፣ ነቀምቴ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚወስደው ዋና መንገድ በመሆኑ የግንባታው መጠናቀቅ የሚኖረውን የኢኮኖሚ ትስስር ያሳልጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በሀብታሙ ተክለስላሴ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.