Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ከአፍሪካ ልማት ባንክ ልዑካን ጋር  ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል  ከአፍሪካ ልማት ባንክ ልዑካን ጋር  በጋራ በሚሰሩ ተግባራትና ተያያዥ ጉዳዮች የፋይናንስ ድጋፍ በሚደረግበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱን ተከትሎ ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገፃችው ባሰፈሩት ጽሑፍ፥ በቀጣይ አምስት ዓመታት ለመተግበር እየተዘጋጀ በሚገኘው የአጋርነት ማዕቀፍ ላይ የሀገራችን ዋነኛ የልማት አጋር ከሆነው የአፍሪካ ልማት ባንክ ልዑካን ጋር ጠቃሚ ምክክር አካሂደናል ብለዋል፡፡

ባንኩ በአፍሪካ ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ልማት እና ማህበራዊ እድገት በማበረታታት ድህነትን ለመቀነስ በሚደረገው ርብርብ የማይተካ ሚና እየተጫወተ ነው ያሉት ወይዘሮ ሙፈሪሃት  ኢትዮጵያ  ለነደፈችው የልማት ዕቅድ ስኬትም የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን  አንስተዋል፡፡

በቀጣይ አምስት ዓመታትም ለመተግበር እየተዘጋጀ በሚገኘው የአጋርነት ማዕቀፍ ላይ በክህሎት ልማት፣ በወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በግሉ ዘርፍ ሚና፣ በጋራ በሚሰሩ ተግባራትና ተያያዥ ጉዳዮች የፋይናንስ ድጋፍ የሚደረግበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን አስፍረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.