Fana: At a Speed of Life!

በአንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተውን የዶሮ በሽታ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ ውጤት እያስገኘ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በአንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተውን የዶሮ በሽታ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ ውጤት እያስገኘ መሆኑን፥ በሽታውን ለመከላከል የተቋቋመው ግብር ኃይል ገለጸ፡፡

ሰሞኑን በአዲስ አበባና በቢሸፍቱ በተወሰኑ የዶሮ እርባታ ማዕከላት የተከሰተው የዶሮ በሽታ ወደ ሌሎች የእርባታ ጣቢያዎችና የሀገሪቱ ክፍሎች እንዳይዛመት ግብረ ኃይል ተቋቁሞ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

የተከሰተው የዶሮ በሽታ ተላላፊና ገዳይ በመሆኑ ህብረተሰቡና አርቢው ማህበረሰብ ዶሮዎች ሲሞቱ ወይም ሞተው ከተገኙ መቅበር፣ የህመም ምልክት ያሳዩ ዶሮዎችን ደግሞ ለሰው ምግብነት ከማዋል መቆጠብ እንዲሁም ለተወሰነ ጊዜ የዶሮዎችን ዝውውር በመግታትና ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ ችግሩን መቅረፍ የሚያስችሉ ስራዎች መሆናቸው ተመላክቷል።

በሽታውን ለመቆጣጠር አሁን እየተወሰደ ያለው የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ ውጤታማ መሆኑንና በሽታው የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ሁሉም አካላት የጥንቃቄ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ አሳስበዋል፡፡

የበሽታውን መንስኤና ምንነት ለማጥናት የጥናት ቡድን ተቋቁሞ ናሙና እየተሰባሰበ በመሆኑ ውጤቱ ሲታወቅ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ ሚኒስትር ዴኤታው መናገራቸውንም ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.