Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል የኢንተርፕራይዞች የምርትና አገልግሎት ኢግዚቢሽንና ባዛር ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ የክልሉን የገጠርና ከተማ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የምርትና አገልግሎት ኢግዚቢሽንና ባዛር በወላይታ ሶዶ ከተማ ከፍተዋል።

ከምርትና አገልግሎት ኢግዚቢሽንና ባዛሩ በተጨማሪ የክልሉ የስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤት ጉባኤ እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡

በዝግጅቱ ከርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፋዬ ይገዙ፣ የደቡብ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ስርሞሎ እና ሌሎችም የክልሉ አመራሮች ተገኝተዋል።

በጌትነት ጃርሳ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.