ስፓርት

በፓሪስ ዳይመንድ ሊግ 5 ሺህ ሜትር ውድድር ሰለሞን ባረጋ አሸነፈ

By Melaku Gedif

June 19, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ ዳይመንድ ሊግ በ5 ሺህ ሜትር ውድድር ሰለሞን ባረጋ አሸንፏል፡፡

በወንዶች ምድብ በተካሄደው 5 ሺህ ሜትር የፓሪስ ዳይመንድ ሊግ ውድድር ሰለሞን ባረጋ ርቀቱን በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ÷ሙክታር እድሪስ ደግሞ 3ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡

በምድቡ አዲሱ ይሁኔ 5ኛ ሆኖ ውድድሩን የጨረሰ መሆኑንም ከአትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡