Fana: At a Speed of Life!

” የአገልጋይነት ብቃትንና ዝግጁነትን በማጠናከር ነዋሪዎችን በብቃት እያገለገልን አዲስ አበባን እጅ ለእጅ ተያይዘን እናበለጽጋለን “- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአገልጋይነት ብቃትን እና ዝግጁነትን በማጠናከር ነዋሪዎችን በብቃት እያገለገልን አዲስ አበባ ከተማን እጅ ለእጅ ተያይዘን እናበለጽጋለን አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡
 
“ብቁና ጤናማ አመራር እና ሲቪል ሰርቫንት ለላቀ አገልግሎት ” በሚል መሪ ቃል ከተማ አቀፍ የአመራርና የሲቪል ሰርቫንት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት በመስቀል አደባባይ ተካሂዷል፡፡
 
በመርሐ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ሰራተኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነው የተካሄደው፡፡
 
ከንቲባ አዳነች አዲስ አበባ የፍቅር ፣ የአብሮነት ፣የአንድነት ፣ የመቻቻልና የብልፅግና ከተማ መሆኗን ጠቅሰው÷ይህንን የሚያፀናው አመራሮች በትጋት ማገልገላችን በመሆኑ ለህዝባችን ቃል የገባነውን በብቃት ውጤት እንድናስቀጥል በአደራ ጭምር ላሳስብ እወዳለሁ ብለዋል ።
 
አዲስ አበባ የፍቅር፤ የአብሮነት እና የአንድነት ከተማ ናት ያሉት ክንቲባዋ÷የአገልጋይነት ብቃትን እና ዝግጁነትን በማጠናከር ነዋሪዎችን በብቃት እያገለገልን አዲስ አበባ ከተማን እጅ ለእጅ ተያይዘን እናበለጽጋለን ብለዋል፡፡
 
 
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ሂክማ ኬይረዲን በበኩላቸው÷ በከተማ ደረጃ ፈጣን ፣ ቀልጣፋና ጊዜ ቆጣቢ አገልግሎት ለተገልጋይ ምላሽ ለመስጠት ብሩህ ፣ ጤናማ ፣ ንቁ አእምሮና የዳበረ አካል ያለው ሲቪል ሰርቫንት መፍጠር ስለሚገባ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባህሉ ያደረገ ሰራተኛ ሊኖር ይገባል ብለዋል፡፡
 
ጤናማ አስተሳሰብና ብቁ አካል በመያዝ ለህዝባችን የምንሰጣቸው አገልግሎት የተቀላጠፈና ውጤታማ በመሆኑ አገልጋይነታችንን ለማረጋገጥ ቃል የምንገባትም ቀን ነው ማለታቸውንም ከአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ያገነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.